am_tw/bible/kt/circumcise.md

10 lines
1.4 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# መገረዝ፣ ግዝረት
“መግረዝ” ከወንድ ወይም ወንድ ከሆነ ትንሽ ልጅ ብልት ትርፍ የሆነውን ቆዳ መቊረጥ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የግርዘት ሥርዓት ሊኖርም ይችላል።
* ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዶን ቤተ ሰብ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድና አገልጋይ እንዲገረዝ እግዚአብሔር አብርሃምን አዝዞት ነበር።
* ቤተ ሰባቸው ውስጥ የሚወለድ ማንኛውንም ወንድ እንዲገርዙ እግዚአብሔር የአብርሃም ዘሮችንም አዝዞአቸዋል።
* “የልብ መገረዝ” የሚለው ሐረግ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ከሰው፣ ኃጢአት “መቆረጥን” ወይም፣ “መወገድን” ያመለክታል።
* በመንፈሳዊ ይዘቱ፣ “የተገረዙ” ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ከኃጢአት ያነጻቸውንና የእርሱ ሕዝብ የሆኑትን ሰዎች ያመለክታል።
* “ያልተገረዙ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የብልት ሥጋቸው ያልተገረዘ ሰዎችን ነው። ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ ያልተገረዙትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸውን ያመለክታል።