# መገረዝ፣ ግዝረት “መግረዝ” ከወንድ ወይም ወንድ ከሆነ ትንሽ ልጅ ብልት ትርፍ የሆነውን ቆዳ መቊረጥ ማለት ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የግርዘት ሥርዓት ሊኖርም ይችላል። * ከእነርሱ ጋር ያደረገው ኪዳን ምልክት እንዶን ቤተ ሰብ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድና አገልጋይ እንዲገረዝ እግዚአብሔር አብርሃምን አዝዞት ነበር። * ቤተ ሰባቸው ውስጥ የሚወለድ ማንኛውንም ወንድ እንዲገርዙ እግዚአብሔር የአብርሃም ዘሮችንም አዝዞአቸዋል። * “የልብ መገረዝ” የሚለው ሐረግ ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ ከሰው፣ ኃጢአት “መቆረጥን” ወይም፣ “መወገድን” ያመለክታል። * በመንፈሳዊ ይዘቱ፣ “የተገረዙ” ማለት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እግዚአብሔር ከኃጢአት ያነጻቸውንና የእርሱ ሕዝብ የሆኑትን ሰዎች ያመለክታል። * “ያልተገረዙ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የብልት ሥጋቸው ያልተገረዘ ሰዎችን ነው። ምሳሌያዊ በሆነ መልኩ በመንፈሳዊ ደረጃ ያልተገረዙትን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የሌላቸውን ያመለክታል።