13 lines
1.1 KiB
Markdown
13 lines
1.1 KiB
Markdown
# ልጆች፣ ልጅ
|
|
|
|
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።
|
|
|
|
* አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ወይም ተከታዮች፣ “ልጆች” በመባል ተጠርተዋል።
|
|
* የአንድን ሰው ዘሮች ለማመልከት፣ “ልጆች” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
|
|
* “የ. . .ልጆች” የሚለው ሐረግ የአንድን ነገር ባሕርይ መያዝ ያመለክታል። የሚከተሉት ለዚህ ምሳሌ ይሆናሉ፤
|
|
* የብርሃን ልጆች
|
|
* የመታዘዝ ልጆች
|
|
* የዲያብሎስ ልጆች
|
|
|
|
ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።
|