am_tw/bible/kt/children.md

1.1 KiB

ልጆች፣ ልጅ

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።

  • አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ወይም ተከታዮች፣ “ልጆች” በመባል ተጠርተዋል።
  • የአንድን ሰው ዘሮች ለማመልከት፣ “ልጆች” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
  • “የ. . .ልጆች” የሚለው ሐረግ የአንድን ነገር ባሕርይ መያዝ ያመለክታል። የሚከተሉት ለዚህ ምሳሌ ይሆናሉ፤
  • የብርሃን ልጆች
  • የመታዘዝ ልጆች
  • የዲያብሎስ ልጆች

ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።