# ልጆች፣ ልጅ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት። * አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ወይም ተከታዮች፣ “ልጆች” በመባል ተጠርተዋል። * የአንድን ሰው ዘሮች ለማመልከት፣ “ልጆች” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል። * “የ. . .ልጆች” የሚለው ሐረግ የአንድን ነገር ባሕርይ መያዝ ያመለክታል። የሚከተሉት ለዚህ ምሳሌ ይሆናሉ፤ * የብርሃን ልጆች * የመታዘዝ ልጆች * የዲያብሎስ ልጆች ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።