am_tw/bible/kt/bond.md

14 lines
2.1 KiB
Markdown

# ማሰር፣ ማሰሪያ፣ አሰረ
“ማሰር” አንድን ነገር ጥብቅ አድርጎ ማሰር ወይም እንዳይበታተን አድርጎ መቋጠር ማለት ነው። አንድ ነገር የሚያስር ወይም እርስ በርስ የሚያያይዝ፣ “ማሰሪያ” ይባላል።
* “አሰረ” የሚባለው አንድ ነገር ሲታሰር ወይም ዙሪያውን ሲጠመጠምበት ነው።
* “ማሰሪያ” ማንኛውንም የሚያስር ነገር ይመለከታል። ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ማሰሪያ ከመንቀሳቀስ የሚያግድ ሰንሰለትን፣ ገመድን፣ ጠፍርን ወይም ሌላ ነገርን ያመለክታል።
* መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ገመዶች ወይም ሰንሰለቶች እስረኞችን ከግድግዳ ወይም ከወለል ጋር አጣብቆ ለመያዝ ያገለግሉ ነበር።
* “ማሰር” የሚለው ቃል ቁስሉ እንዲፈወስ ለመርዳት ቁስሉን በጨርቅ መጠቅለሉን ለመናገር ያገለግል ነበር።
* የሞተ ሰውን ለቀብር ለማዘጋጀት በጨርቅ “ይታሰር” ወይም ይጠቀለል ነበር።
* “ማሰሪያ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር አንድ ሰው የሚቆጣጠር ወይም ባርያ የሚያደርግ ኃጢአትን የመሳሰሉ ነገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
* ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ በሆነ ሁኔታ ሰዎች እንዲረዳዱ በመካከላቸው ያለው ጥብቅ ግንኙነትም ማሰሪያ ሊባል ይችላል። ይህ በጋብቻ መተሳሰርንም ይመለከታል።
* ለምሳሌ ባልና ሚስት እርስ በርስ፣ “ተሳስረዋል” ወይም ተጣምረዋል። ይህ እግዚአብሔር እንዲላቀቅ የማይፈልገው ትስስር ወይም ጥምረት ነው።
* አንድ ሰው በመሐላ “ይታሰራል”፤ ይህም ማለት የገባውን ቃል፣ “የመፈጸም ግዴታ” አለበት ማለት ነው፥