# ማሰር፣ ማሰሪያ፣ አሰረ “ማሰር” አንድን ነገር ጥብቅ አድርጎ ማሰር ወይም እንዳይበታተን አድርጎ መቋጠር ማለት ነው። አንድ ነገር የሚያስር ወይም እርስ በርስ የሚያያይዝ፣ “ማሰሪያ” ይባላል። * “አሰረ” የሚባለው አንድ ነገር ሲታሰር ወይም ዙሪያውን ሲጠመጠምበት ነው። * “ማሰሪያ” ማንኛውንም የሚያስር ነገር ይመለከታል። ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ማሰሪያ ከመንቀሳቀስ የሚያግድ ሰንሰለትን፣ ገመድን፣ ጠፍርን ወይም ሌላ ነገርን ያመለክታል። * መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ገመዶች ወይም ሰንሰለቶች እስረኞችን ከግድግዳ ወይም ከወለል ጋር አጣብቆ ለመያዝ ያገለግሉ ነበር። * “ማሰር” የሚለው ቃል ቁስሉ እንዲፈወስ ለመርዳት ቁስሉን በጨርቅ መጠቅለሉን ለመናገር ያገለግል ነበር። * የሞተ ሰውን ለቀብር ለማዘጋጀት በጨርቅ “ይታሰር” ወይም ይጠቀለል ነበር። * “ማሰሪያ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር አንድ ሰው የሚቆጣጠር ወይም ባርያ የሚያደርግ ኃጢአትን የመሳሰሉ ነገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። * ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ በሆነ ሁኔታ ሰዎች እንዲረዳዱ በመካከላቸው ያለው ጥብቅ ግንኙነትም ማሰሪያ ሊባል ይችላል። ይህ በጋብቻ መተሳሰርንም ይመለከታል። * ለምሳሌ ባልና ሚስት እርስ በርስ፣ “ተሳስረዋል” ወይም ተጣምረዋል። ይህ እግዚአብሔር እንዲላቀቅ የማይፈልገው ትስስር ወይም ጥምረት ነው። * አንድ ሰው በመሐላ “ይታሰራል”፤ ይህም ማለት የገባውን ቃል፣ “የመፈጸም ግዴታ” አለበት ማለት ነው፥