am_tw/bible/kt/bond.md

2.1 KiB

ማሰር፣ ማሰሪያ፣ አሰረ

“ማሰር” አንድን ነገር ጥብቅ አድርጎ ማሰር ወይም እንዳይበታተን አድርጎ መቋጠር ማለት ነው። አንድ ነገር የሚያስር ወይም እርስ በርስ የሚያያይዝ፣ “ማሰሪያ” ይባላል።

  • “አሰረ” የሚባለው አንድ ነገር ሲታሰር ወይም ዙሪያውን ሲጠመጠምበት ነው።
  • “ማሰሪያ” ማንኛውንም የሚያስር ነገር ይመለከታል። ብዙውን ጊዜ አንድን ሰው ማሰሪያ ከመንቀሳቀስ የሚያግድ ሰንሰለትን፣ ገመድን፣ ጠፍርን ወይም ሌላ ነገርን ያመለክታል።
  • መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ገመዶች ወይም ሰንሰለቶች እስረኞችን ከግድግዳ ወይም ከወለል ጋር አጣብቆ ለመያዝ ያገለግሉ ነበር።
  • “ማሰር” የሚለው ቃል ቁስሉ እንዲፈወስ ለመርዳት ቁስሉን በጨርቅ መጠቅለሉን ለመናገር ያገለግል ነበር።
  • የሞተ ሰውን ለቀብር ለማዘጋጀት በጨርቅ “ይታሰር” ወይም ይጠቀለል ነበር።
  • “ማሰሪያ” የሚለው ቃል በምሳሌያዊ አነጋገር አንድ ሰው የሚቆጣጠር ወይም ባርያ የሚያደርግ ኃጢአትን የመሳሰሉ ነገሮችን ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
  • ስሜታዊ፣ መንፈሳዊና አካላዊ በሆነ ሁኔታ ሰዎች እንዲረዳዱ በመካከላቸው ያለው ጥብቅ ግንኙነትም ማሰሪያ ሊባል ይችላል። ይህ በጋብቻ መተሳሰርንም ይመለከታል።
  • ለምሳሌ ባልና ሚስት እርስ በርስ፣ “ተሳስረዋል” ወይም ተጣምረዋል። ይህ እግዚአብሔር እንዲላቀቅ የማይፈልገው ትስስር ወይም ጥምረት ነው።
  • አንድ ሰው በመሐላ “ይታሰራል”፤ ይህም ማለት የገባውን ቃል፣ “የመፈጸም ግዴታ” አለበት ማለት ነው፥