am_tw/bible/kt/boast.md

10 lines
1.4 KiB
Markdown

# መመካት፣ ትምክህተኛ
“መመካት” በሰዎች ወይም በነገሮች በመመካት በትዕቢት መናገር ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ስለ አራስ በእብሪት መናገር ማለት ነው።
* “ትምክህተኛ” ሰው ስለ ራሱ በትዕቢት ይናገራል።
* በጣዖቶቻቸው በመመካታቸው እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገሥጾአል። በእውነተኛው አምላክ ይልቅ በግትርነት ጣዖቶቻቸውን እያመለኩ ነበር።
* መጽሐፍ ቅዱስ ሀብትን፣ ብርታትን፣ ፍሬያማ እርሻንና ሕጎቻቸውን በመሳሰሉ ነገሮች ስለሚመኩ ሰዎችም ይናገራል። ይህም ማለት እነዚህን ነገሮች የሚሰጥ እግዚአብሔር መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ፣ በእነዚህ ነገሮች ትዕቢት አድሮባቸዋል ማለት ነው።
* በእነዚህ ነገሮች ከመመካት ወይም ከመታመን ይልቅ እርሱን በማወቃቸው እንዲመኩ እግዚአብሔር አጥብቆ ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።
* ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ ስለ መመካት ይናገራል፤ ይህም ማለት እርሱ ስላደረገላቸው ሁሉ በእርሱ ደስ መሰኘትና እርሱን ማመስገን ማለት ነው።