1.4 KiB
1.4 KiB
መመካት፣ ትምክህተኛ
“መመካት” በሰዎች ወይም በነገሮች በመመካት በትዕቢት መናገር ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ስለ አራስ በእብሪት መናገር ማለት ነው።
- “ትምክህተኛ” ሰው ስለ ራሱ በትዕቢት ይናገራል።
- በጣዖቶቻቸው በመመካታቸው እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገሥጾአል። በእውነተኛው አምላክ ይልቅ በግትርነት ጣዖቶቻቸውን እያመለኩ ነበር።
- መጽሐፍ ቅዱስ ሀብትን፣ ብርታትን፣ ፍሬያማ እርሻንና ሕጎቻቸውን በመሳሰሉ ነገሮች ስለሚመኩ ሰዎችም ይናገራል። ይህም ማለት እነዚህን ነገሮች የሚሰጥ እግዚአብሔር መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ፣ በእነዚህ ነገሮች ትዕቢት አድሮባቸዋል ማለት ነው።
- በእነዚህ ነገሮች ከመመካት ወይም ከመታመን ይልቅ እርሱን በማወቃቸው እንዲመኩ እግዚአብሔር አጥብቆ ለእስራኤላውያን ተናግሮአል።
- ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ ስለ መመካት ይናገራል፤ ይህም ማለት እርሱ ስላደረገላቸው ሁሉ በእርሱ ደስ መሰኘትና እርሱን ማመስገን ማለት ነው።