# መመካት፣ ትምክህተኛ “መመካት” በሰዎች ወይም በነገሮች በመመካት በትዕቢት መናገር ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ ስለ አራስ በእብሪት መናገር ማለት ነው። * “ትምክህተኛ” ሰው ስለ ራሱ በትዕቢት ይናገራል። * በጣዖቶቻቸው በመመካታቸው እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ገሥጾአል። በእውነተኛው አምላክ ይልቅ በግትርነት ጣዖቶቻቸውን እያመለኩ ነበር። * መጽሐፍ ቅዱስ ሀብትን፣ ብርታትን፣ ፍሬያማ እርሻንና ሕጎቻቸውን በመሳሰሉ ነገሮች ስለሚመኩ ሰዎችም ይናገራል። ይህም ማለት እነዚህን ነገሮች የሚሰጥ እግዚአብሔር መሆኑን ከመገንዘብ ይልቅ፣ በእነዚህ ነገሮች ትዕቢት አድሮባቸዋል ማለት ነው። * በእነዚህ ነገሮች ከመመካት ወይም ከመታመን ይልቅ እርሱን በማወቃቸው እንዲመኩ እግዚአብሔር አጥብቆ ለእስራኤላውያን ተናግሮአል። * ሐዋርያው ጳውሎስ በጌታ ስለ መመካት ይናገራል፤ ይህም ማለት እርሱ ስላደረገላቸው ሁሉ በእርሱ ደስ መሰኘትና እርሱን ማመስገን ማለት ነው።