am_tw/bible/kt/ark.md

1.8 KiB

ታቦት

  • የቃል ኪዳኑ ታቦት፥ የኪዳኑ ሕግ ታቦት፥ የያህዌ (እግዚአብሔር) ታቦት፥ እነዚህ ቃሎች ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የያዘ በወርቅ የተለበጠ ይተለየ የእንጨት ሳጥን ያመለክታሉ። የአሮን በትርና መና የነበረበትንም ዕቃ ይይዛል።
  • እዚህ ላይ፥ “ታቦት” የሚለው፥ “ሳጥን” ወይም፥ “ሰንዱቅ” ወይም፥ “መያዣ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
  • በዚህ ሳጥን ወይም ሰንዱቅ ውስጥ ያሉ ነገሮች ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ያስታውሷቸዋል።
  • የኪዳኑ ታቦት የሚቀመጠው፥ “ቅድስተ ቅዱሳን” ውስጥ ነበር
  • የእግዚአብሔር ሐልዎት ወይም መገኘት ቅድስት ቅዱስን ውስጥ ካለው ከታቦቱ በላይ ነበር፤ እስራኤላውያንን በተመለከተ ለሙሴ የሚናገረው ከዚያ ነበር
  • የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤተ መቅደሱ ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን በነበረበት ዘመን በዓመት አንዴ በስርዓት ቀን ወደታቦቱ መቅረብ የሚችል ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር።
  • አንዳንድ ትርጉሞች፥ የኪዳኑ ታቦት የሚለውን ቃል በቃል፥ “የምስክሩ ታቦት” በማለት ተርጉመውታል። ይህ የሚያመለክተው አሥሩ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን ምስክር ከመሆናቸው አንጻር ነው “ የሕጉ ኪዳን” ተብሎም ተተርጉሟል።