# ታቦት * የቃል ኪዳኑ ታቦት፥ የኪዳኑ ሕግ ታቦት፥ የያህዌ (እግዚአብሔር) ታቦት፥ እነዚህ ቃሎች ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የያዘ በወርቅ የተለበጠ ይተለየ የእንጨት ሳጥን ያመለክታሉ። የአሮን በትርና መና የነበረበትንም ዕቃ ይይዛል። * እዚህ ላይ፥ “ታቦት” የሚለው፥ “ሳጥን” ወይም፥ “ሰንዱቅ” ወይም፥ “መያዣ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። * በዚህ ሳጥን ወይም ሰንዱቅ ውስጥ ያሉ ነገሮች ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ያስታውሷቸዋል። * የኪዳኑ ታቦት የሚቀመጠው፥ “ቅድስተ ቅዱሳን” ውስጥ ነበር * የእግዚአብሔር ሐልዎት ወይም መገኘት ቅድስት ቅዱስን ውስጥ ካለው ከታቦቱ በላይ ነበር፤ እስራኤላውያንን በተመለከተ ለሙሴ የሚናገረው ከዚያ ነበር * የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤተ መቅደሱ ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን በነበረበት ዘመን በዓመት አንዴ በስርዓት ቀን ወደታቦቱ መቅረብ የሚችል ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር። * አንዳንድ ትርጉሞች፥ የኪዳኑ ታቦት የሚለውን ቃል በቃል፥ “የምስክሩ ታቦት” በማለት ተርጉመውታል። ይህ የሚያመለክተው አሥሩ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን ምስክር ከመሆናቸው አንጻር ነው “ የሕጉ ኪዳን” ተብሎም ተተርጉሟል።