am_tw/bible/kt/ark.md

10 lines
1.8 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# ታቦት
* የቃል ኪዳኑ ታቦት፥ የኪዳኑ ሕግ ታቦት፥ የያህዌ (እግዚአብሔር) ታቦት፥ እነዚህ ቃሎች ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸው ሁለት የድንጋይ ጽላቶች የያዘ በወርቅ የተለበጠ ይተለየ የእንጨት ሳጥን ያመለክታሉ። የአሮን በትርና መና የነበረበትንም ዕቃ ይይዛል።
* እዚህ ላይ፥ “ታቦት” የሚለው፥ “ሳጥን” ወይም፥ “ሰንዱቅ” ወይም፥ “መያዣ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
* በዚህ ሳጥን ወይም ሰንዱቅ ውስጥ ያሉ ነገሮች ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ያስታውሷቸዋል።
* የኪዳኑ ታቦት የሚቀመጠው፥ “ቅድስተ ቅዱሳን” ውስጥ ነበር
* የእግዚአብሔር ሐልዎት ወይም መገኘት ቅድስት ቅዱስን ውስጥ ካለው ከታቦቱ በላይ ነበር፤ እስራኤላውያንን በተመለከተ ለሙሴ የሚናገረው ከዚያ ነበር
* የቃል ኪዳኑ ታቦት ቤተ መቅደሱ ውስጥ በነበረው ቅድስተ ቅዱሳን በነበረበት ዘመን በዓመት አንዴ በስርዓት ቀን ወደታቦቱ መቅረብ የሚችል ሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር።
* አንዳንድ ትርጉሞች፥ የኪዳኑ ታቦት የሚለውን ቃል በቃል፥ “የምስክሩ ታቦት” በማለት ተርጉመውታል። ይህ የሚያመለክተው አሥሩ ትእዛዞች እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ኪዳን ምስክር ከመሆናቸው አንጻር ነው “ የሕጉ ኪዳን” ተብሎም ተተርጉሟል።