am_tw/bible/kt/adoption.md

825 B

ልጅነት/ልጅ አድርጎ መቀበል

“ልጅነት” የተሰኘው ቃል አንድን ሰው በተፈጥሮ ወላጆቹ ያልሆኑ ሰዎች ሕጋዊ ልጅ የማድረግ ሂደት ያመለክታል።

  • መጽሐፍ ቅዱስ “ልጅነት” ወይም “ልጅ አድርጎ መውሰድ” የተሰኙትን ቃሎች እግዚአብሔር ሰዎችን እንዴት የቤተሰብ አካል፣የእርሱ መንፈሳዊ ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንደሚያደርግ ለመግለጽ በምሳሌያዊ መልኩ ይጠቀምበታል።
  • ልጆች እንደሆኑ ተቀባይነት በመግኘታቸው አማኞች የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች መብት ሁሉ ያላቸው ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሾች ሆነዋል።