am_tw/bible/other/word.md

10 lines
1.1 KiB
Markdown

# ቃል
“ቃል” አንድ ሰው የተናገረውን ያመለክታል።
* ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን፣ “ቃሌን አላመንህምና” በማለት መልአኩ ለዘካርያስ የተናገረው ነው፤ እንዲህ ማለቱ፣ “የነገርሁህን አላመንህም” ማለቱ ነበር።
* አብዛኛውን ጊዜ ይህ አንድን ቃል ብቻ ሳይሆን መላውን መልእክት ያመለክታል።
* ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቃል”እግዚአብሔር የተናገረውን ወይም ያዘዘውን ሁሉ ይመለከታል፤ “የእግዚአብሔር ቃል” ወይም፣ “የእውነት ቃል” እንደ ተሰኙት።
* አንዳንዴ፣ “ቃል” አጠቃላዩን ንግግር ያመለክታል፣ ለምሳሌ፣ “በቃልና በሥራ የበረታ እንደሚለው። ይህ “በንግግሩም ሆነ በጸባዩ ብርቱ የሆነ” ማለት ነው።
* ይህ ቃል በጣም በተለየ ሁኔታ ጥቅም ላይ የዋለው ኢየሱስ፣ “ቃል” በመባሉ ነው።