# ቃል “ቃል” አንድ ሰው የተናገረውን ያመለክታል። * ለዚህ ምሳሌ የሚሆነን፣ “ቃሌን አላመንህምና” በማለት መልአኩ ለዘካርያስ የተናገረው ነው፤ እንዲህ ማለቱ፣ “የነገርሁህን አላመንህም” ማለቱ ነበር። * አብዛኛውን ጊዜ ይህ አንድን ቃል ብቻ ሳይሆን መላውን መልእክት ያመለክታል። * ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቃል”እግዚአብሔር የተናገረውን ወይም ያዘዘውን ሁሉ ይመለከታል፤ “የእግዚአብሔር ቃል” ወይም፣ “የእውነት ቃል” እንደ ተሰኙት። * አንዳንዴ፣ “ቃል” አጠቃላዩን ንግግር ያመለክታል፣ ለምሳሌ፣ “በቃልና በሥራ የበረታ እንደሚለው። ይህ “በንግግሩም ሆነ በጸባዩ ብርቱ የሆነ” ማለት ነው። * ይህ ቃል በጣም በተለየ ሁኔታ ጥቅም ላይ የዋለው ኢየሱስ፣ “ቃል” በመባሉ ነው።