am_tw/bible/other/terror.md

11 lines
965 B
Markdown

# ሽብር፣ ማሽበር
“ሽብር” የሚለው ቃል በጣም የመፍራትና የመደንገጥ ስሜት ወይም አንድን ሰው ወይም ነገር በጣም መጥላት ማለት ነው።
* በጣም የሚያስፈራ ወይም የሚያስጠላ ነገርም ሽብር ሊሆን ይችላል።
* ወደ ፊት እየገሠገሠ ያለ አጥቂ ሰራዊት ጠላቶቹ ላይ ሽብር ያሳድራል።
* አንድ ቀን እግዚአብሔር የሚያመጣው ፍርድ ጸጋውን የሚንቁትን ሁሉ ያሸብራል።
* “የያህዌ ሽብር” የሚለው፣ “አስፈሪው የያህዌ ሕልሞች” ወይም፣ “አስፈሪው የያህዌ ፍርድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
* አንድን ሰው፣ “ማሸበር” እጅግ በጣም እንዲፈራ ማድረግ ማለት ነው።
* “የሚያሸብር” ነገር ሁሉ ፍርሃትና ድንጋጤ ያመጣል።