# ሽብር፣ ማሽበር “ሽብር” የሚለው ቃል በጣም የመፍራትና የመደንገጥ ስሜት ወይም አንድን ሰው ወይም ነገር በጣም መጥላት ማለት ነው። * በጣም የሚያስፈራ ወይም የሚያስጠላ ነገርም ሽብር ሊሆን ይችላል። * ወደ ፊት እየገሠገሠ ያለ አጥቂ ሰራዊት ጠላቶቹ ላይ ሽብር ያሳድራል። * አንድ ቀን እግዚአብሔር የሚያመጣው ፍርድ ጸጋውን የሚንቁትን ሁሉ ያሸብራል። * “የያህዌ ሽብር” የሚለው፣ “አስፈሪው የያህዌ ሕልሞች” ወይም፣ “አስፈሪው የያህዌ ፍርድ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። * አንድን ሰው፣ “ማሸበር” እጅግ በጣም እንዲፈራ ማድረግ ማለት ነው። * “የሚያሸብር” ነገር ሁሉ ፍርሃትና ድንጋጤ ያመጣል።