am_tw/bible/other/scepter.md

9 lines
886 B
Markdown

# በትረ መንግሥት
“በትረ መንግሥት” አንድ ንጉሥ ወይም የአገር አስተዳዳሪ የሚይዘው ጌጠኛ በትር ወይም ዱላ ነው
* መጀመሪያ ላይ በተረ መንግሥት የሚሠራው ጌጣ ጌጦች ከተቀረጹበት የዛፍ ቅርንጫፍ ነበር። በኋላ ግን ወርቅን ከመሳሰሉ የከበሩ ድንጋዮችም ይሠራ ጀመር
* በትረ መንግሥት ከንጉሡ ጋር የተያያዘውን ክብርና ታላቅነት የሚያሳይ የንጉሣዊነትና የሥልጣን ምልክት ነው
* ብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር የጽድቅ በትር እንዳለው ይናገራል
* የብሉይ ኪዳን ትንቢት መንግሥታትን ለመግዛት ክርስቶስ ከእስራኤል እንደበትረ መንግሥት እንደሚወጣ ያመለክታል