am_tw/bible/other/sacrifice.md

1.6 KiB
Raw Permalink Blame History

መሥዋዕት፣ ቁርባን

“ቁርባን” (ስጦታ) የሚለው ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የተሰጠ ማንኛውንም ነገር የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው። መሥዋዕት በብዙ መልኩ ይመሳሰላል፤ ሆኖም በተለምዶ ከተገደሉ በኋላ ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የሚሰጡ ነገሮችን ያመለክታል

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምንመለከታቸው ቁርባኖችና መሥዋዕቶች እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሰጡ ነበሩ
  • የተለያዩ ብዙ ዐይነት መሥዋዕትና ቁርባኖች እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ከስእራኤላውያን ይጠብቅ ነበር። ይህም እግዚአብሔር ኅጢአትን ይቅር እንዲል የሚቀርብ ቁርባንን፣ ስለ በረከቱ እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚቀርብ ቁርባንን ይጨምራል። ከእነዚህ ቁርባኖች ጥቂቶቹ፣ “የሚቃጠል መሥዋዕት” “የኅጢአት መሥዋዕት” “የእህል መሥዋዕት” እና፣ “የመጠጥ መሥዋዕት” ናቸው
  • የመሥዋዕቶቹ ስም መሠረት የሚሆነው መሥዋዕት የሚሆነውን ነገርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ዓላማ ነው
  • የሰዎችን ኅጢአት ፈጽሞ የሚያነጻ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ያዘጋጀው መሥዋዕት ብቻ ነው። የእንስሳት ደም መሥዋዕት ያንን ማድረግ አይችልም