9 lines
1.6 KiB
Markdown
9 lines
1.6 KiB
Markdown
|
# መሥዋዕት፣ ቁርባን
|
|||
|
|
|||
|
“ቁርባን” (ስጦታ) የሚለው ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የተሰጠ ማንኛውንም ነገር የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው። መሥዋዕት በብዙ መልኩ ይመሳሰላል፤ ሆኖም በተለምዶ ከተገደሉ በኋላ ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የሚሰጡ ነገሮችን ያመለክታል
|
|||
|
|
|||
|
* መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምንመለከታቸው ቁርባኖችና መሥዋዕቶች እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሰጡ ነበሩ
|
|||
|
* የተለያዩ ብዙ ዐይነት መሥዋዕትና ቁርባኖች እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ከስእራኤላውያን ይጠብቅ ነበር። ይህም እግዚአብሔር ኅጢአትን ይቅር እንዲል የሚቀርብ ቁርባንን፣ ስለ በረከቱ እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚቀርብ ቁርባንን ይጨምራል። ከእነዚህ ቁርባኖች ጥቂቶቹ፣ “የሚቃጠል መሥዋዕት” – “የኅጢአት መሥዋዕት” – “የእህል መሥዋዕት” እና፣ “የመጠጥ መሥዋዕት” ናቸው
|
|||
|
* የመሥዋዕቶቹ ስም መሠረት የሚሆነው መሥዋዕት የሚሆነውን ነገርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ዓላማ ነው
|
|||
|
* የሰዎችን ኅጢአት ፈጽሞ የሚያነጻ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ያዘጋጀው መሥዋዕት ብቻ ነው። የእንስሳት ደም መሥዋዕት ያንን ማድረግ አይችልም
|