# መሥዋዕት፣ ቁርባን “ቁርባን” (ስጦታ) የሚለው ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የተሰጠ ማንኛውንም ነገር የሚያመለክት አጠቃላይ ቃል ነው። መሥዋዕት በብዙ መልኩ ይመሳሰላል፤ ሆኖም በተለምዶ ከተገደሉ በኋላ ለእግዚአብሔር ወይም ለጣዖት የሚሰጡ ነገሮችን ያመለክታል * መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የምንመለከታቸው ቁርባኖችና መሥዋዕቶች እግዚአብሔርን ለማምለክ የተሰጡ ነበሩ * የተለያዩ ብዙ ዐይነት መሥዋዕትና ቁርባኖች እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር ከስእራኤላውያን ይጠብቅ ነበር። ይህም እግዚአብሔር ኅጢአትን ይቅር እንዲል የሚቀርብ ቁርባንን፣ ስለ በረከቱ እግዚአብሔርን ለማመስገን የሚቀርብ ቁርባንን ይጨምራል። ከእነዚህ ቁርባኖች ጥቂቶቹ፣ “የሚቃጠል መሥዋዕት” – “የኅጢአት መሥዋዕት” – “የእህል መሥዋዕት” እና፣ “የመጠጥ መሥዋዕት” ናቸው * የመሥዋዕቶቹ ስም መሠረት የሚሆነው መሥዋዕት የሚሆነውን ነገርና መሥዋዕቱ የሚቀርብበት ዓላማ ነው * የሰዎችን ኅጢአት ፈጽሞ የሚያነጻ እግዚአብሔር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ያዘጋጀው መሥዋዕት ብቻ ነው። የእንስሳት ደም መሥዋዕት ያንን ማድረግ አይችልም