am_tw/bible/other/harp.md

9 lines
710 B
Markdown

# በገና
በገና ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ ክሮች ወይም ገመዶች ይኖሩታል።
* የጥድ እንጨት በገናና ሌሎች የሙዚቃ መሣሪያዎች ለመሥራት ያገለግላል።
* በጥንት ዘመን በገና ብዙውን ጊዜ በእጅ ተይዞ መንገድ ሲሄዱ የሚጫወቱት ነበር።
* ብዙውን ጊዜ በገና ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነበር።
* ዳዊት በገና ሲደረድር ንጉሥ ሳኦል ከጭንቀት መንፈስ ፋታ ያገኝ ነበር። በበገና የተዜሙ በርካታ መዝሙሮችንም ጽፎአል።