በገና
በገና ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ ክሮች ወይም ገመዶች ይኖሩታል።
- የጥድ እንጨት በገናና ሌሎች የሙዚቃ መሣሪያዎች ለመሥራት ያገለግላል።
- በጥንት ዘመን በገና ብዙውን ጊዜ በእጅ ተይዞ መንገድ ሲሄዱ የሚጫወቱት ነበር።
- ብዙውን ጊዜ በገና ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነበር።
- ዳዊት በገና ሲደረድር ንጉሥ ሳኦል ከጭንቀት መንፈስ ፋታ ያገኝ ነበር። በበገና የተዜሙ በርካታ መዝሙሮችንም ጽፎአል።