# በገና በገና ባለ ገመድ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን፣ ቀጥ ያሉ ክሮች ወይም ገመዶች ይኖሩታል። * የጥድ እንጨት በገናና ሌሎች የሙዚቃ መሣሪያዎች ለመሥራት ያገለግላል። * በጥንት ዘመን በገና ብዙውን ጊዜ በእጅ ተይዞ መንገድ ሲሄዱ የሚጫወቱት ነበር። * ብዙውን ጊዜ በገና ጥቅም ላይ የሚውለው እግዚአብሔርን ለማመስገን ነበር። * ዳዊት በገና ሲደረድር ንጉሥ ሳኦል ከጭንቀት መንፈስ ፋታ ያገኝ ነበር። በበገና የተዜሙ በርካታ መዝሙሮችንም ጽፎአል።