ዋሽንት
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋሽንት ከአጥንትና ከእንጨት የሚሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን ድምፅ እንዲያወጣ መተላለፊያዎች ይሠሩለትም ነበር።
- ብዙውን ጊዜ እረኞች ራሳቸውን ዘና ለማድረግና እንስሶቻቸውንም ለማረጋጋት ዋሽንት ይጫወቱ ነበር።
- በጥንቱ ቤተ መቅደስ በዝማሬ አገልግሎት ዋሽንት ጥቅም ላይ ይውል ነበር።
- ንጉሥ ናቡከደነፆር ለጣኦቶቹ ክብር ሰዎች እንዲጫወቱ ካዘዛቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነበር።