# ዋሽንት መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ዋሽንት ከአጥንትና ከእንጨት የሚሠራ የሙዚቃ መሣሪያ ሲሆን ድምፅ እንዲያወጣ መተላለፊያዎች ይሠሩለትም ነበር። * ብዙውን ጊዜ እረኞች ራሳቸውን ዘና ለማድረግና እንስሶቻቸውንም ለማረጋጋት ዋሽንት ይጫወቱ ነበር። * በጥንቱ ቤተ መቅደስ በዝማሬ አገልግሎት ዋሽንት ጥቅም ላይ ይውል ነበር። * ንጉሥ ናቡከደነፆር ለጣኦቶቹ ክብር ሰዎች እንዲጫወቱ ካዘዛቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነበር።