am_tw/bible/other/festival.md

16 lines
1.0 KiB
Markdown

# በኣል
አጠቃላይ በሆነ መልኩ በኣል የማኅበረሰቡ ሰዎች በአንድነት የሚያከብሩት ሁኔታ ነው።
* በብሉይ ኪዳን መሠረት፣ “በዓል” ቃል በቃል፣ “የተወሰነ ወይም የተመደበ ቀን” ማለት ነው።
* እስራኤላውያን የሚያከብሯቸው በዓሎች እግዚአብሔር እንዲጠብቁት ባዘዛቸው መሠረት በተለየ ሁኔታ የተመደበ ጊዜ ወይም ወቅት ናቸው።
* እስራኤላውያን በየዓመቱ የሚያከብሯቸው ዋና ዋና በዓሎች አሉ፤
* የፋሲካ በዓል
* የቂጣ በዓል
* የመከር በዓል
* በዓለ-ሃምሳ
* የመለከት በዓል
* የስርየት በዓል
* የዳስ በዓል
* የእነዚህ በዓሎች ዓላማ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ሕዝቡን ለመታደግ፣ ለመጠበቅና የሚያስፈልገውን በመስጠት ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ለማስታወስ ነው።