# በኣል አጠቃላይ በሆነ መልኩ በኣል የማኅበረሰቡ ሰዎች በአንድነት የሚያከብሩት ሁኔታ ነው። * በብሉይ ኪዳን መሠረት፣ “በዓል” ቃል በቃል፣ “የተወሰነ ወይም የተመደበ ቀን” ማለት ነው። * እስራኤላውያን የሚያከብሯቸው በዓሎች እግዚአብሔር እንዲጠብቁት ባዘዛቸው መሠረት በተለየ ሁኔታ የተመደበ ጊዜ ወይም ወቅት ናቸው። * እስራኤላውያን በየዓመቱ የሚያከብሯቸው ዋና ዋና በዓሎች አሉ፤ * የፋሲካ በዓል * የቂጣ በዓል * የመከር በዓል * በዓለ-ሃምሳ * የመለከት በዓል * የስርየት በዓል * የዳስ በዓል * የእነዚህ በዓሎች ዓላማ እግዚአብሔርን ለማመስገንና ሕዝቡን ለመታደግ፣ ለመጠበቅና የሚያስፈልገውን በመስጠት ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ለማስታወስ ነው።