am_tw/bible/other/donkey.md

10 lines
898 B
Markdown

# አህያ፣ በቅሎ
አህያ ከፈረስ የሚያንስና ትላልቅ ጆሮዎች ያሉ ፈረስን የሚመስል ባለ አራት እግር አገልጋይ እንስሳ ነው።
* በቅሎ ከወንድ አህያና ከሴት ፈረስ የምትወለድ መሐን እንስሳ ናት።
* በቅሎዎች ብርቱ እንስሳት በመሆናቸው ለተለያየ አገልግሎት ከፍ ያለ ጥቅም አላቸው።
* አህዮችና በቅሎዎች ዕቃዎችንና ሰዎን ለመሸከም ያገልግላሉ።
* መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በሰላም ጊዜ ንጉሦች ያሚጓዙት በአህያ ሲሆን፣ በጦርነት ጊዜ የሚጓዙት በፈረስ ነበር።
* ከመስቃሉ አንድ ሳምንት በፊት ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ነበር።