# አህያ፣ በቅሎ አህያ ከፈረስ የሚያንስና ትላልቅ ጆሮዎች ያሉ ፈረስን የሚመስል ባለ አራት እግር አገልጋይ እንስሳ ነው። * በቅሎ ከወንድ አህያና ከሴት ፈረስ የምትወለድ መሐን እንስሳ ናት። * በቅሎዎች ብርቱ እንስሳት በመሆናቸው ለተለያየ አገልግሎት ከፍ ያለ ጥቅም አላቸው። * አህዮችና በቅሎዎች ዕቃዎችንና ሰዎን ለመሸከም ያገልግላሉ። * መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን በሰላም ጊዜ ንጉሦች ያሚጓዙት በአህያ ሲሆን፣ በጦርነት ጊዜ የሚጓዙት በፈረስ ነበር። * ከመስቃሉ አንድ ሳምንት በፊት ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በአህያ ውርንጭላ ተቀምጦ ነበር።