am_tw/bible/other/desert.md

9 lines
847 B
Markdown

# በረሐ፣ ምድረ በዳ
በረሐ ወይም ምድረ በዳ በጣም ጥቂት ተክሎችና ዛፎች ብቻ የሚያድጉበት ደረቅና ጠፍ ቦታ ነው።
* በረሐ ጥቂት ተክሎች ወይም እንስሳት ያሉት ደረቅ የአየር ፀባይ ያለው አካባቢ ነው።
* እንዲህ ያለው ቦታ በጣም አስቸጋሪ በመሆኑ በረሐ ውስጥ የሚኖሩ በጣም ጥቂት ሰዎች ናቸው። ይህ ቦታ፣ “ምድረ በዳ” ተብሎም ይጠራል።
* “ምድረ በዳ” ሲባል በጣም ሩቅ፣ የተተወና ከሰዎች መኖሪያ የተገለለ የሚል ዐሳብ አለው።
* ይህ ቃል፣ “ሰው የማይኖርበት” ወይም፣ “ሩቅ ቦታ” ወይም “የተተወ ቦታ” ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።