am_tw/bible/other/curtain.md

8 lines
1.1 KiB
Markdown

# መጋረጃ
መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን “መጋረጃ” የሚያመለክተው መገናኛው ድንኳንንና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ወፍራምና በጣም ከባድ ጨርቅ ነበር።
* መገናኛው ድንኳን የተሠራው ከላይና ከጎን በተዘረጉ አራት ተደራራቢ መጋረጃዎች ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከጨርቅ ወይም ከእንስሳት ቆዳ ይሠሩ ነበር።
* የጨርቅ መጋረጃዎች በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ዙሪያ ግድግዳ በመሆን ያገለግሉ ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከተልባ እግር ማለትም ከናይለንም ይሠሩ ነበር።
* በመገናኛው ድንኳንም ሆነ በቤተ መቅደሱ ግንባታ ሥራ በቅድስተ ቅዱሳኑና በተቀደሰው ቦታ መካከል በጣም ትልቅ የጨርቅ መጋረጃ ይደረግ ነበር። ኢየሱስ መስቀል ላይ በሞተ ጊዜ በተአምር ለሁለት የተቀደደው ይኸው መጋረጃ ነበር።