# መጋረጃ መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን “መጋረጃ” የሚያመለክተው መገናኛው ድንኳንንና ቤተ መቅደሱን ለመሥራት ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን ወፍራምና በጣም ከባድ ጨርቅ ነበር። * መገናኛው ድንኳን የተሠራው ከላይና ከጎን በተዘረጉ አራት ተደራራቢ መጋረጃዎች ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከጨርቅ ወይም ከእንስሳት ቆዳ ይሠሩ ነበር። * የጨርቅ መጋረጃዎች በመገናኛው ድንኳን አደባባይ ዙሪያ ግድግዳ በመሆን ያገለግሉ ነበር። እነዚህ መጋረጃዎች ከተልባ እግር ማለትም ከናይለንም ይሠሩ ነበር። * በመገናኛው ድንኳንም ሆነ በቤተ መቅደሱ ግንባታ ሥራ በቅድስተ ቅዱሳኑና በተቀደሰው ቦታ መካከል በጣም ትልቅ የጨርቅ መጋረጃ ይደረግ ነበር። ኢየሱስ መስቀል ላይ በሞተ ጊዜ በተአምር ለሁለት የተቀደደው ይኸው መጋረጃ ነበር።