1.4 KiB
1.4 KiB
አደባባይ፣ ችሎት
“አደባባይ” ዙሪያውን የተከበበና ከላይ በኩል ክፍት የሆነ ገላጣ አካባቢ ነው።
- “ችሎት” ዳኞች ፍትሕ ብሔርና ወንጀል ነክ ነገሮችን የሚዳኙበት ቦታ ማለት ነው።
- መገናኛው ድንኳን በወፍራም የጨርቅ መጋረጃዎች ግድግዳነት በታጠረ አንድ አደባባይ ተከብቦ ነበር።
- የቤተ መቅደሱ ሕንፃ ሦስት የውስጥ አደባባዮች ነበሩት፤ አንዱ ለካህናት፣ አንዱ ለአይሁዳውያን ወንዶችና ሌላው ደግሞ ለአይሁዳውያን ሴቶች።
- አነዚህ የውስጥ አደባባይች አሕዛብ እንዲያመልኩ ከተፈቀደበት ውጫዊ አደባባይ የሚለያቸው በቁመት ዝቅ ያሉ የድንጋይ ግድግዳ ነበራቸው።
- የአንድ ቤት አደባባይ ቤቱ መካከል ላይ ያለ ግልጥ ቦታ ነው።
- “የንጉሥ ችሎት” የሚለው ሐረግ ቤተ መንግሥቱን ወይም ፍርድ የሚሰጥበትን ቦታ ሊያመለክት ይችላል።
- “ይያህዌ አደባባይ” ይያህዌ መኖሪያን ወይም ሰዎች ያህዌን ለማምለክ የሚሰጡበት ቦታን የሚያመለክት ምሳሌያዊ አንጋገር ነው።