936 B
936 B
የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በእሳት መሠዋት
“የሚቃጠል መሥዋዕት” የሚባለው መሠዊያው ላይ በእሳት ተቃጥሎ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ዐይነት ነው። የሚቃጠለው ለሕዝቡ ኀጢአት ስርየት ለመሆን ነው። “በእሳት መሠዋት” ተብሎም ይጠራል።
- ለዚህ መሥዋዕት የሚቀርብ እንስሳት ብዙውን ጊዜ በጎችና ፍየሎች ቢሆኑም፣ በሬዎችና ወፎችም መሥዋዕት ይሆናሉ።
- የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ከቆዳው ውጪ የእንስሳው አካል በሙሉ ይቃጠላል። ቆዳው ወይም ሌጦው ለካህኑ ይሰጠዋል።
- በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ አዝዞ ነበር።