# የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በእሳት መሠዋት “የሚቃጠል መሥዋዕት” የሚባለው መሠዊያው ላይ በእሳት ተቃጥሎ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ዐይነት ነው። የሚቃጠለው ለሕዝቡ ኀጢአት ስርየት ለመሆን ነው። “በእሳት መሠዋት” ተብሎም ይጠራል። * ለዚህ መሥዋዕት የሚቀርብ እንስሳት ብዙውን ጊዜ በጎችና ፍየሎች ቢሆኑም፣ በሬዎችና ወፎችም መሥዋዕት ይሆናሉ። * የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ከቆዳው ውጪ የእንስሳው አካል በሙሉ ይቃጠላል። ቆዳው ወይም ሌጦው ለካህኑ ይሰጠዋል። * በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ አዝዞ ነበር።