am_tw/bible/other/burntoffering.md

8 lines
936 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-04 19:07:37 +00:00
# የሚቃጠል መሥዋዕት፣ በእሳት መሠዋት
“የሚቃጠል መሥዋዕት” የሚባለው መሠዊያው ላይ በእሳት ተቃጥሎ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ዐይነት ነው። የሚቃጠለው ለሕዝቡ ኀጢአት ስርየት ለመሆን ነው። “በእሳት መሠዋት” ተብሎም ይጠራል።
* ለዚህ መሥዋዕት የሚቀርብ እንስሳት ብዙውን ጊዜ በጎችና ፍየሎች ቢሆኑም፣ በሬዎችና ወፎችም መሥዋዕት ይሆናሉ።
* የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ከቆዳው ውጪ የእንስሳው አካል በሙሉ ይቃጠላል። ቆዳው ወይም ሌጦው ለካህኑ ይሰጠዋል።
* በዓመት ሁለት ጊዜ የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲያቀርቡ እግዚአብሔር የአይሁድን ሕዝብ አዝዞ ነበር።