am_tw/bible/other/blemish.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown

# እንከን፣ ነውር
“እንከን” ወይም ነውር አንድ እንስሳ ወይም ሰው ላይ ያለ ጉድለትን ወይም ሙሉ ያለመሆንን ያመለክታል። ሰዎች ላይ ያለ በደልን ወይም መንፈሳዊ ጉድለትንም ያመለክታል።
* አንዳንድ መሥዋዕቶችን በተመለከተ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲናገር እንከን ወይም ነውር የሌለበትን እንስሳ እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቷል።
* ይህ ሥዕል ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ኃጢአት የሌለው ፍጹም መሥዋዕት መሆኑን ያመለክታል።
* በክርስቶስ የሚያምኑ አማኞች በእርሱ ደም ከኃጢአታቸው ነጸተዋል፤ ስለዚህም እንከን ወይም ነውር የሌለባቸው ተብለዋል።
* እንደ ዐውደ ምንባቡ ይህን፣ “ጉድለት” ወይም፣ “ነቀፋ” ወይም፣ “ኃጢአት” በማለት መተርጎም ይቻላል።