# እንከን፣ ነውር “እንከን” ወይም ነውር አንድ እንስሳ ወይም ሰው ላይ ያለ ጉድለትን ወይም ሙሉ ያለመሆንን ያመለክታል። ሰዎች ላይ ያለ በደልን ወይም መንፈሳዊ ጉድለትንም ያመለክታል። * አንዳንድ መሥዋዕቶችን በተመለከተ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲናገር እንከን ወይም ነውር የሌለበትን እንስሳ እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቷል። * ይህ ሥዕል ኢየሱስ ክርስቶስ ምንም ኃጢአት የሌለው ፍጹም መሥዋዕት መሆኑን ያመለክታል። * በክርስቶስ የሚያምኑ አማኞች በእርሱ ደም ከኃጢአታቸው ነጸተዋል፤ ስለዚህም እንከን ወይም ነውር የሌለባቸው ተብለዋል። * እንደ ዐውደ ምንባቡ ይህን፣ “ጉድለት” ወይም፣ “ነቀፋ” ወይም፣ “ኃጢአት” በማለት መተርጎም ይቻላል።