am_tw/bible/names/zadok.md

9 lines
713 B
Markdown

# ሳዶቅ
ሳዶቅ በንጉሥ ዳዊት ዘመን በእስራኤል የነበረ ሁነኛ ሊቀ ካህን ነበር።
* አቤሴሎም ባመፀበት ጊዜ ሳዶቅ ዳዊትን ደግፎ ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጣ ዳዊትን የረዳው እርሱ ነበር።
* ከዓመታት በኋላ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ እንዲሆን ሲቀባ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝቶ ነበር።
* በነህምያ ዘመን የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲሠራ ሳዶቅ የተባሉ ሁለት ሰዎች ረድተው ነበር።
* የንጉሥ ኢዮአታም አያት ስም ሳዶቅ ይባል ነበር።