# ሳዶቅ ሳዶቅ በንጉሥ ዳዊት ዘመን በእስራኤል የነበረ ሁነኛ ሊቀ ካህን ነበር። * አቤሴሎም ባመፀበት ጊዜ ሳዶቅ ዳዊትን ደግፎ ነበር፤ የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያመጣ ዳዊትን የረዳው እርሱ ነበር። * ከዓመታት በኋላ የዳዊት ልጅ ሰሎሞን ንጉሥ እንዲሆን ሲቀባ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝቶ ነበር። * በነህምያ ዘመን የኢየሩሳሌም ቅጥር ሲሠራ ሳዶቅ የተባሉ ሁለት ሰዎች ረድተው ነበር። * የንጉሥ ኢዮአታም አያት ስም ሳዶቅ ይባል ነበር።