am_tw/bible/names/simonthezealot.md

9 lines
1.0 KiB
Markdown

# ቀናተኛው ስምዖን
ቀናተኛው ስምዖን ከአሥራ ሁለት የኢየሱስ የቅርብ ደቀመዛሙርት አንዱ ነበር
* ስለ ቀናተኛው ስምዖን የሚታወቀው በጣም ጥቂት ነው። በኢየሱስ ደቀመዛሙርት ዝርዝር ውስጥ ሦስቴ ተጠቅሷል
* ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ በአንድነት ከተሰበሰቡት አሥራ አንድ ደቀመዛሙርት አንዱ ስምዖን ነበር
* አንዳንድ ሰዎች፣ “ቀናተኛው” የሚለው የሚያመለክተው ስምዖን የሙሴን ሕግ በመጠበቅ ረገድ በጣም ቀናተኛ የነበሩና የሮም መንግሥትን አጥብቀው የሚቃወሙ፣ “ቀናተኞች” የሚባለው የአይሁድ ሃይማኖት ቡድን አባል ነበር በማለት ያስባሉ
* ሌሎች ደግሞ፣ “ቀናተኛ” የሚለው የስምዖንን ሃይማኖታዊ ቅንዓት ለማመልከት ብቻ ነው ይላሉ