# ቀናተኛው ስምዖን ቀናተኛው ስምዖን ከአሥራ ሁለት የኢየሱስ የቅርብ ደቀመዛሙርት አንዱ ነበር * ስለ ቀናተኛው ስምዖን የሚታወቀው በጣም ጥቂት ነው። በኢየሱስ ደቀመዛሙርት ዝርዝር ውስጥ ሦስቴ ተጠቅሷል * ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ በአንድነት ከተሰበሰቡት አሥራ አንድ ደቀመዛሙርት አንዱ ስምዖን ነበር * አንዳንድ ሰዎች፣ “ቀናተኛው” የሚለው የሚያመለክተው ስምዖን የሙሴን ሕግ በመጠበቅ ረገድ በጣም ቀናተኛ የነበሩና የሮም መንግሥትን አጥብቀው የሚቃወሙ፣ “ቀናተኞች” የሚባለው የአይሁድ ሃይማኖት ቡድን አባል ነበር በማለት ያስባሉ * ሌሎች ደግሞ፣ “ቀናተኛ” የሚለው የስምዖንን ሃይማኖታዊ ቅንዓት ለማመልከት ብቻ ነው ይላሉ