am_tw/bible/names/rome.md

9 lines
780 B
Markdown

# ሮም፣ ሮማዊ
በዚህ ባለንበት ዘመን ሮም የኢጣልያ ዋና ከተማ ናት።
* ኢየሱስና ሐዋርያቱ ባገለገሉበት ዘመን ሮም የሮም መንግሥት ማዕከል ነበረች።
* የሮም መንግሥት እስራኤልን ጨምሮ ሜዲትራንያን ባሕር ዙሪያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር።
* “ሮማዊ” የሚለው ቃል ሮማውያን ዜጎችንና ባለ ሥልጣኖችን ጨምሮ የሮም መንግሥት ከሚገዛው አካባቢ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ሁሉ ያመለክታል።
* ሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሱስን የምሥራች በመስበኩ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ከተማ ተወስዶ ነበር።