# ሮም፣ ሮማዊ በዚህ ባለንበት ዘመን ሮም የኢጣልያ ዋና ከተማ ናት። * ኢየሱስና ሐዋርያቱ ባገለገሉበት ዘመን ሮም የሮም መንግሥት ማዕከል ነበረች። * የሮም መንግሥት እስራኤልን ጨምሮ ሜዲትራንያን ባሕር ዙሪያ የነበረውን አካባቢ ሁሉ ይገዛ ነበር። * “ሮማዊ” የሚለው ቃል ሮማውያን ዜጎችንና ባለ ሥልጣኖችን ጨምሮ የሮም መንግሥት ከሚገዛው አካባቢ ጋር የተያያዙ ነገሮችን ሁሉ ያመለክታል። * ሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሱስን የምሥራች በመስበኩ እስረኛ ሆኖ ወደ ሮም ከተማ ተወስዶ ነበር።