am_tw/bible/names/ramoth.md

8 lines
781 B
Markdown

# ራሞት
ራሞት ገለዓድ ተራሮች ላይ የምትገኝ በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ራሞት ገለዓድም ትባላለች።
* ራሞት የጋድ ድርሻ ነበረች፤ የመማጸኛ ከተማም ነበረች።
* የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ከአራም ንጉሥ ጋር የተዋጉት በራሞት ነበር። አክዓብ በጦርነቱ ተገደለ።
* በኋላ ላይ ንጉሥ አካዝያስና ንጉሥ ኢዮራም ከአራም ንጉሥ ራሞትን ለመውሰድ ሞክረው ነበር፤ ሆንም ንጉሥ ኢዮራም ቆሰለ። የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን በራሞት ተቀብቶ በነበረው በኢዩ ሁለቱም ተገደሉ።