# ራሞት ራሞት ገለዓድ ተራሮች ላይ የምትገኝ በጣም ጠቃሚ ከተማ ነበረች። ራሞት ገለዓድም ትባላለች። * ራሞት የጋድ ድርሻ ነበረች፤ የመማጸኛ ከተማም ነበረች። * የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ከአራም ንጉሥ ጋር የተዋጉት በራሞት ነበር። አክዓብ በጦርነቱ ተገደለ። * በኋላ ላይ ንጉሥ አካዝያስና ንጉሥ ኢዮራም ከአራም ንጉሥ ራሞትን ለመውሰድ ሞክረው ነበር፤ ሆንም ንጉሥ ኢዮራም ቆሰለ። የእስራኤል ንጉሥ እንዲሆን በራሞት ተቀብቶ በነበረው በኢዩ ሁለቱም ተገደሉ።