am_tw/bible/names/priscilla.md

10 lines
860 B
Markdown

# ጵርስቅላ
ጵርስቅላ ከባልዋ ከአቂላ ጋር በሐዋርያዊ ተልዕኮው ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር አብራ ትሠራ የነበረች የመጀመሪያው መቶኛ ዓመት አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች።
* ጳውሎስ አቂላና ጵርስቅላን ያገኘው በቆሮንቶስ ነበር።
* አቂላና ጵርስቅላ ለጊዜው በሮም ኖረዋል።
* ባልና ሚስቱ ከጳውሎስ ጋር ድንኳን ይሰፉ ነበር፤ በሐዋርያዊ ሥራውም ይረዱት ነበር።
* አቂላና ጵርስቅላ የጳውሎስ ረዳቶች መሆናቸው አዲስ ኪዳን ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል።
* ጵርስቅላ በጥንት ቤተ ክርስቲያን የነበረች ሴት መምህር መሆንዋ እንደ ምሳሌ ይጠቀሳል።